What's Happening ?

Get Events Throughout Addis!

event image

የስዕል ደብተሬ

1 week ago  /Eaglopia

“የስዕል ደብተሬ” የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

በምዕራፍ ግሩም የተዘጋጀው “የስዕል ደብተሬ” የተሰኘ የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ የህፃናት መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይመረቃል።

መፅሃፉ ለኢትዮጵያውያን ልጆች የተዘጋጀ ሃብታም ከሆነው ባህላቸውና ታሪካቸው የሚያቀራርባቸው፣ የሚያጭውት፣ የሚያዝናና እንዲሁም የታዳጊዎችን የመፍጠር ችሎታ የሚያሳድግና  እውቀት የሚሰጣቸው ብቻ ሳይሆን ስነምግባር የሚያስተምር ፣መረዳዳትንና መዋደድን የሚመክር ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን አዘጋጇ ለሸገር ታይምስ ሚዲያ ገልጻለች፡፡

የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ ግንቦት 11 ቀን ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል  እንደሚደረግና ወላጆች በምርቃት ቦታ ከልጆቻቻው ጋር በመገኘት ልጆቻቻውን እያስተማሩና እያዝናኑ ለኢትዮጵያ ልጆች  ጠቃሚና ገንቢ ተደርገው የተዘጋጁትን መጻሕፍት እንዲመርቁም  አዘጋጆቹ ምዕራፍ  ግሩምና ፈንድቃ የባህል ማእከል ጥሪ  አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አዲስ ከሚመረቀው "የስዕል ደብተሬ" በተጨማሪ በአዘጋጇ ከዚህ ቀደም የተዘጋጀውን በኢትዮጵያን ባህላዊ አልባሳት  የማቅለሚያ መጽሐፍ ቁጥር 1 መጽሐፍ ም የማግኘት እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡